የምንሠራው ሥራ

Developing Medicine በ2021 ያልተመዘገበ ማኅበር ሆኖ የተቋቋመና በ2024 በዩናይትድ ኪንግደም በሕጋዊ ሰውነት የተመዘገበ ሰብዓዊ የሕክምና ድርጅት ነው።

በአሁኑ ጊዜ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ወደ 50 የሚጠጉ ዶክተሮችን፣ ተዛማጅ የጤና ባለሙያዎችንና ተርጓሚዎችን ያቀፈ መረብ ነን።

ዓላማችን በታዳጊ አገሮች የጤና አገልግሎትን ማሻሻል ሲሆን ይህንንም የምናደርገው፦

  • በታዳጊ አገሮች የሕክምና ግብዓቶችን፣ እርዳታንና ድጋፍን በመስጠት (በገንዘብ ድጋፍ (ድጎማ) ፕሮግራማችን በኩልም ጭምር)፤
  • ለታዳጊ አገሮች ሕዝብ ነፃ የዲጂታል የሕክምና መረጃዎችን በማዘጋጀትና በማሰራጨት፣ ይህም በማደግ ላይ ያሉ የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ቴክኖሎጂዎችን የሚያሟሉ ዲጂታል ግብዓቶችን ይጨምራል፤
  • በታዳጊ አገሮች ውስጥ ላሉ ታካሚዎች፣ ስደተኞችና ተፈናቃዮች በመሟገት፤
  • በተመሳሳይ መስኮች የሚሠሩ ሌሎች መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን በመደገፍ ነው።

ስለ እነዚህ ሥራዎች የበለጠ ለማወቅ ከታች ያሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይከተሉ። ድርጅታችን እያደገ ሲሄድ እናዘምናቸዋለን። ስለ ሥራችን ወይም ስለ ድርጅታችን በአጠቃላይ ማንኛውም ጥያቄ ካለዎት «ያግኙን» በሚለው ገጻችን በኩል ያለምንም ማመንታት ያግኙን። በተቻለ ፍጥነት ለመመለስ የተቻለንን ሁሉ እናደርጋለን።