ለስኳር ህመምተኞች የእግር እንክብካቤ

ዶክተሮቻችን የስኳር ህመምተኞች ለምን በእግራቸው ላይ ችግር እንደሚያጋጥማቸው እና የእነዚህን ችግሮች ስጋት ለመቀነስ ምን ማድረግ እንደሚችሉ ያብራራሉ.

የስኳር በሽታ እግርን ለምን ሊጎዳ ይችላል

የስኳር በሽታ የመዳሰስ ስሜት የሚሰጡንን ነርቮች ይጎዳል፤ ብዙውን ጊዜ ቀድመው የሚጎዱት እግሮች ናቸው። ስለዚህ እግርዎ ቢቆረጥ፣ ቢቃጠል ወይም ቢጎዳ፣ ወይም ቁስሉ ቢመረዝ ላያስተውሉ ይችላሉ። የተመረዘ ቁስል የእግር ጣቶችን፣ እግርን ወይም የእግርን የተወሰነ ክፍል ወደ መቆረጥ ሊያደርስ፤ ሕይወትንም አደጋ ላይ ሊጥል ይችላል።

እግርዎን የሚጠብቁባቸው ስድስት መንገዶች

  1. እግርዎን በየጊዜው ይመርምሩ፤ በጣቶች መካከልና ከሥር ጭምር። ትንሽ መስታወት ይጠቀሙ ወይም የሌላ ሰው እርዳታ ይጠይቁ። መቆረጥ፣ መሰንጠቅና ኮርን ይፈልጉ፤ ካገኙም ንጹሕና ደረቅ ያድርጓቸው።
  2. የእግር ጥፍርዎን በጥንቃቄ ይቁረጡ፤ ቆዳዎን እንዳይወጋ።
  3. የማይፈትጉና የማያጣብቁ ምቹ ጫማዎችን ከላላ ምቹ ካልሲ ጋር ያድርጉ።
  4. በፍጹም በባዶ እግር አይሂዱ፤ በተለይ እንደ ሲሚንቶ ወይም አሸዋ ባሉ ሞቃት ቦታዎች ላይ።
  5. የደደረ ቆዳን (ካሉስ) ራስዎ አያስወግዱ። ሊመረዝ ይችላል። የጤና ባለሙያ ያማክሩ።
  6. ቁስሉ የተመረዘ መስሎ ከታየዎት በተቻለ ፍጥነት የጤና ባለሙያ ያማክሩ። የመመረዝ ምልክቶች መቅላት፣ መግል እና እየጨመረ የሚሄድ ሕመም ናቸው።

ማሳሰቢያ: ይህ መረጃ ለአጠቃላይ ትምህርት ብቻ ነው። የጤና ባለሙያን ምክር አይተካም። ስለ ጤናዎ ስጋት ካለዎት ወይም ምልክቶችዎ እየባሱ ከሄዱ የጤና ባለሙያ ያማክሩ። በድንገተኛ ሁኔታ ወዲያውኑ በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ የጤና ተቋም ይሂዱ።

ምንጮች

  • NHS (UK): Complications – peripheral neuropathy
  • NHS (UK): Looking after your diabetic foot ulcer to reduce the risk of amputation
  • WHO: Prevention and management of diabetic foot problems

ስለዚህ መረጃ

ዶክተሮቻችን እያንዳንዱን መረጃ ይጽፋሉ፤ ይገመግማሉም። መረጃዎቻችንን እንዴት እንደምናዘጋጅ

ስህተት ካዩ እባክዎ በኢሜይል ያሳውቁን፦ doctors@developingmedicine.org

ተዛማጅ መረጃ

በአማርኛ ያሉ ሁሉም የጤና መረጃዎቻችን