ስድስት የተለመዱ የጡት ካንሰር ምልክቶች

በአማርኛ የሚናገሩ ዶክተሮቻችን ስድስት የተለመዱ የጡት ካንሰር ምልክቶችን ያብራራሉ።

ቀድሞ ማወቅ ለምን አስፈላጊ ነው

የጡት ካንሰር በዓለም ዙሪያ በሴቶች ላይ ለሚደርስ ሕመምና ሞት ዋነኛ ምክንያት ነው። የዓለም ጤና ድርጅት እንደሚለው፣ ከ12 ሴቶች መካከል አንዷ በሕይወት ዘመኗ የጡት ካንሰር ይገኝባታል። እንደ እድል ሆኖ፣ በተለይ ቀድሞ ከተገኘ ብዙውን ጊዜ ሊታከም ይችላል።

ስድስት የተለመዱ ምልክቶች

  1. በጡት፣ በደረት ወይም በብብት ላይ እብጠት ወይም ጠጣር ነገር። በየጊዜው ራስዎን ይመርምሩ። ሌላ ምክንያት ሊኖረው ይችላል፤ ነገር ግን የጤና ባለሙያ ይመርምረው።
  2. የጡት ቆዳ ለውጥ፣ ለምሳሌ ቆዳው መሰርጎድ (የብርቱካን ልጣጭ መምሰል) ወይም መቅላት። በጠቆረ ቆዳ ላይ እነዚህን ማየት ይከብድ ይሆናል።
  3. የአንዱ ወይም የሁለቱም ጡቶች መጠን ወይም ቅርጽ ያለምክንያት መለወጥ።
  4. ከጡት ጫፍ ፈሳሽ መውጣት፣ እርጉዝ ሳይሆኑ ወይም ሳያጠቡ፣ በተለይ ደም ከቀላቀለ።
  5. የጡት ጫፍ ለውጥ፣ ለምሳሌ ጫፉ ወደ ውስጥ መግባት ወይም ሽፍታ።
  6. የማይጠፋ የጡት ወይም የብብት ሕመም። እየመጣ የሚሄድ ሕመም ብዙውን ጊዜ የጡት ካንሰር ምልክት አይደለም።

ከእነዚህ ምልክቶች አንዱ መኖሩ የግድ የጡት ካንሰር አለብዎት ማለት አይደለም። ነገር ግን ማንኛውንም ካስተዋሉ በተቻለ ፍጥነት የጤና ባለሙያ ያማክሩ፤ ጡትዎንም በየጊዜው ይመርምሩ።

ማሳሰቢያ: ይህ መረጃ ለአጠቃላይ ትምህርት ብቻ ነው። የጤና ባለሙያን ምክር አይተካም። ስለ ጤናዎ ስጋት ካለዎት ወይም ምልክቶችዎ እየባሱ ከሄዱ የጤና ባለሙያ ያማክሩ። በድንገተኛ ሁኔታ ወዲያውኑ በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ የጤና ተቋም ይሂዱ።